ለሱዳን የተሰጠው መሬት መዘዝ እየወለደ መጣ |
|
![]() |
ለሱዳን የተቸረው የኢትዮጵያ መሬት |
ኢትዮጵያ ዛሬ፡ የወያኔ አገዛዝ በሰሜን ምእራብ በኩል የሚገኘውን የኢትዮጵያን መሬት ገምድሎ ለሱዳን የሰጠው መሬት የአካባቢውን ነዋሪ ኢትዮጵያዊ እያስቆጣው ሄዱአል። ባልተጠበቀ ሁኔታም ነዋሪው ህዝብ የራሱን ርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአይን እማኞች አስታወቁ።
ኢትዮጵያውያኑ የወያኔን ባለስልጣናትን የፖለቲካ ውሳኔ በመቃወም ሰሞኑን በወሰዱት ርምጃ ቦታው የኢትዮጵያ እንጂ የሱዳናውያን አይደለም በማለት መሬቱ ላይ የብረት ችካል ተክለው “ይህ ኢትዮጵያ ድንበር ነው” በማለት ከዚህ አንድ ክንድ መሬት አልፎ የመጣ በአካባቢው ሕዝብ ላይ የጦርነት ክተት ማወጅ ነው በማለት ተመልሰዋል ተብሉአል።
ዛሬ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ የምትገኘውን ባድመን አልሰጥም በማለት እየሞገተየአማራ ክልልን ለም መሬት ለሱዳን መሰጠት አማራውን መናቅ ነው በማለት የአካባቢው ተወላጆች በምሬት በግልፅ ሲናገሩ ተስተውለዋል
ከዚህ ጋር ተያይዞም አንዳንድ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ የሞከሩና በወያኔ ችሮታ በኢትዮጵያ ይዞታ ስር በነበረው ቦታ እና ጉዋንግ ከሚባለውን ወንዝ ባሻገር የሱዳናዊያን ቤት በእሳት መጋየቱ ተሰምቱአል። ይህ ሁኔታ በአስቸኩአይ መፍትሄ ካልተበጀለት የወያኔ መሪዎች እንደሚሉት ሰላም ሳይሆን በአካባቢው በቀላሉ የማይበርድ እሳት ያስከትላል ይላሉ እነዚህ እማኞች።