የሬዲዮው ድራማ ውልደትና እድገት
እነማን ለምን ከጀርባ ተሰለፉ?
ኢትዮጵያ ዛሬ-በቅርቡ በቅንጅት የአመራር አባልነት የሚታወቁ ግለሰቦች አቀነባበሩት የተባለ የሬዲዮ ስርጭት ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ በአጭር ሞገድ ለመጀመር የ1.2 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ መጠየቁ ተሰምቱአል።
ይህን ዜና ይፋ ያደረገው የዜና አውታር ጉዳዩን ወደ አደባባይ ይዞ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ በተለያዩ ምክንያቶች በጃችን የገባውን መረጃ በመንተራስ ለአንባብያን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያደረግነው ጥረት ባይሳካም ይፋ የሆነውን ዜና መነሻ በማድረግ ኢትዮ ቱዴይ ካሉአት መረጃዎች ጋር በማያያዝ ለአንባብያን በሚከተለው መልኩ አቀናብረነዋል።
ዜናው በቀዳሚነት ይፋ የሆነው በጠንካራ የመረጃ መረብነቱ በሚታወቀው ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር መሆኑ አይዘነጋም። በዘገባውም እንደተመለከተው ይህ የአጭር ሞገድ የራዲዮ ስርጭት መርሃግብር በዋንኛነት እየተቀነቀነ ያለው በዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ላለፉት ጥቂት አመታት ሲያራግቡት ከነበረው የፖለቲካ ሰፈር ለምን እየወጡ እንደመጡ ከአንደበታቸው የወጣ መግለጫ ባይኖርም የሚደመጡ መላምቶች ግን የሉም ማለት አይቻልም።
ምናልባትም በፖለቲካው ዘርፍ በሌላ አቀራረብ ለመግባት ካላቸው ፍላጎት በተጨማሪ በዋንኛነት ስማቸው ከሚነሳበት የቅንጅት ክፍፍል ባሻገር የነዋይ ጥማቸውን በዝግታ የማውጫ መንገድ እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል የሚሉም ወገኖች አልታጡም።ይህን የሚሉ ወገኖች በዚህ ዙሪያ ያሰባሰቡአቸውን ሰዎች ማንነት በመጥቀስ ይከራከራሉ። ለዚህ ፕሮጀክት ገቢራዊነትም በቃዳሚነት የታጩት ባለፉት ጊዚያት በቅንጀት መሪዎች መሃል ልዩነትን በማራገብና ፊና አበጅተው በአውሮፓና በአሜሪካ አብይ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦች እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በተለይም በዚህ ረገድ ስማቸው የሚነሳ ጥቂት ግለሰቦች ቁልፍ ቦታ ለመያዝ የሚያደርጉት ሩጫ አስረጂ ሆኖ እየቀረበ ነው።የአቶ ብርሃነ መዋና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስም ከሚጠቀሱት ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ ይዞ ይገኛል።
ለዚህ ስራ የሚያስፈልገውን ሁኔታ እንዲያመቻችና ገነዘቡን በስሙ እንዲያስገባ አንድ ትርፋማ ያልሆነ ድርጀት በአውሮፓዊቱአ ሆላንድ እንዲቁቁም ተደርጉአል። ይህን ድርጅት በስማቸው እንዲያቁቁሙ በነዶ/ር ብርሃኑ የታዘዙት በሙሉ በክፍፍሉ ውቅትም ሆነ ቀደም ሲል በነአቶ አንዳርጋቸው በሚመራው የቅንጅት አለማቀፍ አመራር ዘመን በታማኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው። ይህን ደርጀት በማቁቁዋም ረገድ የኢትዮ ሚዲያ ፎረም አዘጋጅ ክንፉ አሰፋ እና በብራሰልስ የኦነግ ተወካይ የነበረው አበበ ቦጋለ በሰም የሚጠቀሱ ሆነዋል። ከነርሱ ጋር ለቡድኑ ታማኝ የሆኑ ግለሰቦችም ተካተዋል።
በአውሮፓ ህብረት በኩል የተጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ የተቃና እንዲሆን በምርጫው ወቅት የህብረቱ የታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩትን ወ/ሮ አና ጎሜዝንና በወቅቱ የህብረቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ የነበሩት ቲሞት ክላርክን የማግባባቱ ስራ ብዙ እንደተገፋበት ለማወቅ ተችሉአል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ይህ የሬዲዮ ስርጭት በተባለው መልኩ የቀረበ ይሁን እንጂ ዝርዝር ፕሮጀክት ፕሮፖዛሉ የተሰረቀ ስለመሆኑ እስካሁን ደፍሮ የተናገረ ባይኖርም ጉዳዩ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የዚህ ዜና ዝግጅት ክፍል ባለው መረጃ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ጥንስስ ከአንድ አመት ተኩል ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ነጻው ፕሬስ ከደረሰበት ችግር አኩአያ አማራጭ ብዙሃን መገናኛ ዘዴ ለመፍጠር በሚል አምስተርዳም ከተማ ላይ በተካሄደ አውደጥናት ላይ ተቀርጾ ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ የተለወጠው እቅድ ነው። ይህ እቅድም ገቢራዊ እንዲሆን በተቁቁዋመው ግብረሃይል ውስጥ በአባልነት የሚገኘው ክንፉ አሰፋ ባልደረቦቹን ከድቶ ከዚህ ቡድን ጋር በጀመረው ሚስጢራዊ ግንኙነት በአጋጣሚው በእጁ የገባውን ፕሮፖዛል ተመሳጥሮ በነጻ ፕሬስ ስም እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለሌላ አላማ አቅርቦታል። ምናልባት ይህ ሚስጢር ሲጋለጥ የሚከተለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ግለሰብ ጋርም ቀደም ሲል ከወያነ ጋዜጠኝነት ተነስቶ ነጻውን ፕሬስ ተቀላቅሎ አሁን ደግሞ በሰሜን አሜሪካ የቅንጅት አመራር አባል ሊሆን የበቃው ዳዊት ከበደም ይገኝበታል ተብሉአል።
በዚህ አሁን በተጀመረው የዶ/ር ብርሃኑ ምስጢራዊ እንቅስቃሴ ቅር የተሰኙ የቅርብ ደጋፊዎቻቸው ቁጥር እየተበራከተ መጥቱአል። በተለይም ቶሎ ወደሃገርቤት ተመልሰን ድርጅቱን እናጠናክራለን በሚል ያሰሙት በነበረው ንግግር ደግፈዋቸው ገንዘብ ሲለግሱአቸው የቆዩ ሁሉ በአሁኑ ወቅት በሁኔታቸው ግራ እየተጋቡ እንደመጡ በስፋት እየተደመጠ ነው። ከዚህ በስተጀርባ በቅርቡ በቡድኑ በኩል ይፋ ይሆናል የሚባለው የቡድኑ አቁዋም ታክሎበት አንዳንድ ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ ዛሬም ያሉአትን የመረጃ ምንጮች በመጠቀም አዳዲስ ክስተቶች የተካተቱበትን ዝርዝር ዘገባ ይዛ በቅርቡ ትቀርባለች።