የሕወሀቱ ታጋይ ስዬ አብርሀ ምስጢራዊ ስብሰባ
ኢትዮጵያ ዛሬ በቨርጂኒያ በአንድ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ ቢሮ ውስጥ የቀድሞው የትግራይ ነፃ አውጪ መከላከያ መሪ አቶ ስዬ አብረሃ በዋሽንግተን የፖለቲካ ተሳትፎ ይታወቃሉ ከተባሉ የተለያዩ የፖለቲካ፤ የሚዲያና ታዋቂ ሰዎች ጋር በምሰጢር መወያየታቸውንየኢትዮጵያ ዛሬ ዜና ወኪል ገለጠ። ከሁለት ሳምንታት በፊት አቶ ስዬ ይፋ ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ ያካሄዱ ቢሆንም ለግለሰቡ ተልዕኮ ይህ የቨርጂኒያው ሚስጢራዊው ግንኙነት የከተማይቱን ዋነኛ ተዋናዮች ለማጠመድ የታሰበ እንደነበረ ተጠርጥሩዋል። አቶ ስዬ አብርሀ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእንግዲህ ሕወሀትን ተዋግታችሁ መመለስ ስለማትችሉ መታረቁ ይሻላችሁዋል የሚል አንድምታ ያለው አነጋገራቸውን አበክረው ሲገልጡ ተሰምተዋል። ይፋ ባልሆነው በዚህ ስብሰባ ከአስራ ሁለት ያላነሱ ሰዎች መገኘታቸውን (ስማቸው አስፈላጊ ሲሆን ይወጣል) ምንጮቻችን ጠቁመው በዋሽንግተን በኢትዮጵያ ጉዳይ <የከረረ> አቁዋም አለው ከሚባለው የነፃነት ለኢትዮጵያ ራዲዮ አቶ አለም ፈቃደ መገኘታቸው ብዙዎችን አስገርሙዋል። ሌሎችን በጥያቄ ለማጠደፍ እንደሚተጉት ሁሉ ስለሁኔታው ነፃነት ራዲዮ እንዲገልጥ የኢትዮጵያ ዜና ያሳስባል።
አቶ ስዬ <ታረቁ> በሚለው መልዕክታቸውና ቅስቀሳቸውን ባደረጉበት በዚያ ዝግ ስብሰባ ውስጥ የነፃነቱን አቶ አለምን ጨምሮ ሀሳባቸውን የሞገቱዋቸው መኖራቸውን መረጃው አስረድቱዋል። የአቶ ስዬ አመጣጥና የቅስቀሳ ሂደት በገዢው ፓርቲ በተገፋው ጎሳ ፖለቲካ ምክንያት የተፈጠረው ፀረ-ትግሬ ስሜትን ለማለዘብ በስልት የተቀነባበረ እንደሚመስል ብዙዎች ይጠረጥራሉ።