የፓርላማው አባል ከዱ - አርበኞች ግንባርን ተቀላቀሉ
ታማኝ ተቃዋሚ በአዲስ አበባ ወያኔን እያጀበ ነው

ኢትዮጵያ ዛሬ ፤- አንድ በወያኔ የበላይነት የሚመራው ፓርማ አባል ለእረፍት ከሄዱበት አገዛዙን በመሳሪያ ኃይል በመታገል ላይ የሚገኘውንና “ አርበኞች ግንባር ” በሚል የሚታወቀውን ወታደራዊ ኃይል ተቀላቀሉ።
ልዑል ከስክስ አስታጥቄ የተባሉት የፓርላማ አባል ከዚህ ውሳኔ ለምን እንደደረሱ በይፋ የሰጡት መግለጫ ባይኖርም አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢ ያነጋገራቸው የፓርላማው አባላት እንደገለጹት በሁሉም ዘንድ መነጋገሪያ መሆኑን አመልክተዋል። ከስፍራው በደረሰን መረጃ መሰረት አቶ ልዑል ግንባሩን የተቀላቀሉት ለእረፍት ወደ ትውልድ ሃገራቸው ጎንደር በሄዱበት ወቅት ነው። ይህንን ጉዳይ በቅርብ ያውቃሉ የሚባሉ የፓርላማው አባላት ለዘጋቢያችን እንደገለጹት ከሆነ በፓርላማው ለወንበር ጌጥ የተቀመጥን ከመሆን ውጪ ከዚያ ያለፈ ሚና ስለሌን የአቶ ልዑል ውሳኔ በብዙዎቻችን አዕምሮ የሚጉላላ ነው ብለዋል።
በፓርላማው መቀመጫውን በጉልበት ነጥቆ ይዞ የሚገኘው የወያኔ አገዛዝ የገዛ አባላቱ በሕዝቡ ዘንድ እየደረሰባቸው በሚገኘው ተቃውሞና ውግዘት በየጊዜው ጥለውት እየሄዱ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ባለፉት ጥቂት አመታት ከሃገር ውስጥ እየኮበለሉ ከሚጠፉት በተጨማሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች በስብሰባ ስም ወደ ተለያዩ ሃገራት ከሚሄዱ የፓርላማ አባላት አብዛኛዎቹ በሄዱበት አገር ጥገኝነት እየጠየቁ በአገዛዙ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ እያሳዩ ናቸው።
ይህ በንዲህ እንዳለ በቅርቡ የወያኔ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጠው አንድ ፓርቲ በመጪው ሚያዚያ በሚካሄደው የአካባቢና የማሙአያ ምርጫ 539 እጩዎችን አቀርባለሁ ማለቱ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ አነጋጋሪ ሆኑአል። ይህ አዲስ ፓርቲ በቅጡ ማደራጀት ቀርቶ የሚያውቀው ሰው እንኩአ ሳይኖር በምርጫው እገባለሁ ማለቱ ወያኔን በማጀብ ውድድር እንደተካሄደ ለማሰኘት ነው ስሉ በርካታ ታዛብልዎች ይተቻሉ።
በይፋ መቁዋቁዋሙ በተገለጠ በጥቂት ቀናት ውስጥ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር በሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች ይህን ማስተወቁን ተከትሎ ያገኘነው መረጃ ፓርቲው የገዢው ፓርቲ ድጋፍ ያልተለየው በታማኝ ተቃዋሚነት የተፈጠረ እንደሆነ ያመለክታል። “የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ንቅናቄ ” በሚል መጠሪያ አዲስ አበባ የተመሰረተው ፓርቲ ፈቃድ ለመጠየቅ ባስገባው ማመልከቻ ያሰባሰበው የድጋፍ ፊርማ በአብዛኛው ከአንድ አካባቢ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የፓርቲውን ሊቀመንበር መስፍን ሽፈራውን በመጥቀስ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮግራሙን እንኩአ የማስተዋወቅ ዕድል ሳያገኝ በአዲስ አበባ ለቀበሌ ም/ ቤት 300 እጩዎችን ፤ ለክልል ም/ቤት 202 ፤ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ደግሞ 37 ከድምሩ 539 እጩዎችን ማዘጋጀቱን የወያኔ ሚዲያዎች በስፋት ዘግበዋል።
ይሁንና ባገኘነው መረጃ መሰረት በዚህ ፓርቲ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች ከአገዛዙ ጋር በመዋወዳጀት ባገኙት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ተወዳዳሪ መስለው ለመቅረብ እየተዘጋጁ እንደሆነ ታውቁአል። ለዚህም በቀዳሚነት ያቀረቡት የምርጫ መተክል ኤች አር 2003 ን መቃወምና በቀበሌ ደረጃ የልማት ሥራ ለመስራት ነው የሚል ነው ። በዚህ ፓርቲ ውስጥ ቀደም ሲል ተካሂዶ በነበረው የግንቦት 1997 ዓ.ም. ምርጫ የኢቶዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረትን ወክለው በሰሜን ጎንደር ተወዳድረው የነበሩት አቶ ጉእሽ ገ/ሥላሴ ፣ ተሻገር ፣ ዓለማየሁና እንደዚሁም ለጊዜው ስማቸው ያልተገለጠ አንዲት ሴት በዋንኛነት በንቅናቄ ውስጥ ስማቸው የሚነሳ ነው።
----------------------------------------------------------------------------------
Dec 20, 2007 www.ethiotoday.net