ወያኔ ኤች አር 2003ን በመቃወም የጠራውን ሰልፍ አካሄደ
ኢትዮጵያ ዛሬ- በኢትዮጵያ የህግ ልዕልናና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ገቢራዊ ይሆን ዘንድ የሚያሳስበውን ረቂቅ ህግ የወያኔ አገዛዝ በመቃውም በካድሬዎቹ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰልፉን ያስተባበሩት የአምባሰደርነት ቦታውን በዚህ ያልተቁረጠ ስራቸው ማግኘት እንደሚፈልጉ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናገረዋል። ይህ አዝማሚያም በአሁኑ ወቅት አምባሳደር በሆኑት በዶ/ርሳሙኤልአሰፋዘንድየተወደደእንዳልሆነተደምጡአል። ረቂቅ ህጉ በሴኔቱ ጸድቆ እንዳይወጣ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደው በኦክሎሆማ ስቴት ነው ። በ Senator James Inhofe ቢሮ ደጃፍ ላይ የተጠራውንና ዲሴምበር 18 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደውን ሰልፍ በማካሄዳቸው በርካታ የወያኔ ሹማምንትእና ካድሬዎች እንደ ትልቅ ስኬት ቆጥረውት በእጅጉ መደሰታቸውን ከአዲስ አበባ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ይህን ሰልፍ ያቀናበረው ሎሳንጀለስ የሚገኘው የወያኔ ቆንስል ታዬ ኅዝቀሥላሴ ከሎሳንጅለስ ወደ ዳላስ ቴክሳስ በመሄድ ከዚያም ወደ ኦክሎሆማ ነድቶ በመሄድ ነው። ተሳታፊዎቹም ከዳላስ ቴክሳስ የመጡ የወያኔ አባላት ደጋፊዎችና በአሁኑ ፖለቲካዊ ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ተቸግረው የቆዩ ጥቂት ኤርትራውያን መሆናቸው ታውቁአል። ኤርትራውያኑ ለዚህ ውለታቸው ታዬ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበተን ሁኔታ እንደሚያመቻችላቸው ቃል ገብቶላቸዋል ተመልክቱአል።
ታዬ ይህን ሰልፍ በሚያዘጋጅበት ወቅትም ቀደም ሲል ወደ ወያኔ ከመቀላቀሉ በፊት የኢህአፓ አባል ሳለ የሚያውቃቸውን የአካባቢውን ተወላጆች እንዲያጅቡት ጠይቆ አሳፍረው መልሰወታል ተብሉአል። በተለይም የጎንደር አካባቢ ተወላጅነቱን ለዚህ እንደ ማግባቢያ ሲጠቀምበት እንደነበር እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል። ታዬ ከዶ/ር ሳሙኤል ይልቅ ለድርጅቱ ታማኝና ተቆርቁሪ ነን በማለት በየአጋጣሚው የሚናገር እንደሆነም በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ።
----------------------------------------------------------------------------
www.ethiotoday.net